Sunday, July 14, 2024
HomeEthiopian Newsሕወሓት /ኢህአዲግን/ ለማፍረስ የተጀመረውን ሕዝባዊ ሃይላችንን እናጠናክር! ለምን?

ሕወሓት /ኢህአዲግን/ ለማፍረስ የተጀመረውን ሕዝባዊ ሃይላችንን እናጠናክር! ለምን?

6. የሐገርን ባህልና ታሪክ ማጥፋት የኢትዮጵያን የ 3000 አመት ታሪክ መካድ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ማቅረብ ታሪክን መበረዝ የፈጠራ ታሪክ መፍጠር የኢትዮጵያን ህዝብ ባህል ስብእና ዕምነት ኩራት ማንነት ብሄራዊ እሴቱን አንድነቱንና ብሄራዊ መገለጫዎቹን ማጥፋት:: የኢትዮጵያን ታሪክ የወያኔን ታሪክ ብቻ አድርጎ በካድሬዎቹና ለጥቅማቸው ባደሩ ተራ ግለሰቦች በገንዘብ እያማለለ ማፃፍ:: ልክ እንደ ውጭ ጠላቶች ኢትዮጵያዊነትን ማዋረድ ማጥላላት ማናናቅና የመሳሰሉትን አስነዋሪ የቅጥረኝነቱን ተግባር እየፈፅመ ይገኛል::
7. የሙስና መስፋፋት

በብሄርና በጎጥ የተደራጁ ጥቂት የወያኔ ማፊያዎች የሌብነት ተግባራቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ለማስፈፅም ዘራፊ ድርጅት በማቋቋም ህዝቡንና ሀገሪቱን መዝረፍ በከፋ ሁኔታ ሕዝብን ማደህየት ለዘመናት ከኖሩበት ስፍራ በማፈናቀል ለርሀብ መዳረግ የበዪ ተመልካች ማድረግ በዘመናዊ ቤት መኖር የብዙ ቤቶች ባለቤት መሆን ዘመናዊ መኪናዎችን መቀያየር በመቶ ሚሊዮኖች የሚገመት ህንፃና ፋብሪካዎች መገንባት ለወያኔ ብቻ የተፈቀደ እስኪመስል ድረስ ማግበስበስ:: በጣም በረቀቀና በአስከፊ ሁኔታ ከሀገርና ከህዝብ የሚዘረፈውን ከፍተኛ ሀብት ከኢትዮጵያ ማሸሽና በተለያዩ የውጭ ሀገር ባንኮች መደበቅ ይህም ሳያንስ በባእዳን ሀገር በቢሊየን የሚቆጥሩ ዶላሮችን አውጥቶ ህንፃ መገንባትን ሥራዬ ብለው ተያይዘውታል::

8. የሚዲያ አፈና የኢትዮጵያ ህዝብ ትክክለኛ እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን እንዳያገኝና በኢኮኖሚ በማህበራዊ በፖለቲካ በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዳይሆን ማድረግ:: እኔ አውቅልሀለው የምነግርህን ብቻ ተቀበል ብሎ ህዝብን በወያኔ የመረጃ ማሰራጫዎቹ ማደንቆር:: ትክክለኛ እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለህዝቡ የሚያደርሱትን የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የመረጃ ተቓማትን ማለትም የግል ጋዜጣዎችን አታሚ ድርጅቶችን መዝጋት ፍቃድ መከልከል ባሰቤቶቹን መስፈራራት ማዋከብ መደብደብ ማሰር ከሀገር እንዲሰደዱ ማድረግ እንዲሁም በሬዲዮ ቴሌቪዥን እና በድህረ ገዕች የሚሰራጩትን መረጃዎች ከፍተኛ ገንዘብ በማውጣት ሞገዳቸውን ማፈን ::

9. ዘመነ ሌጋሲ ከቀድሞ ጠ/ሚ በኃላ ለለውጥ ከመነሳሳት ይልቅ ሐገሪቱን የማፈራረስ እቅዳቸውን በከፍተኛ ሁኔታ የወያኔ ጀሌዎች ተያይዘውታል በሰላማዊ እና በሰለጠነ መልኩ ለውጥ ፈላጊው የኢትዮጽያ ሕዝብ ጥያቄውን ይዞ ቢነሳም ምላሹ ጥይት ማስፈራራት በእስር ቤት መታጎር አሰከፊ የሆነውን ጡንቻቸውንና የበላይነታቸውን ማሳየት በከፍተኛ ሁኔታ ተያይዘውታል ለምሳሌ ሰማያዊ ፓርቲ በቅርቡ ያቀረባቸው ህገመንግስታዊ ጥያቄዎችን ገዢው መንግስት ልክ ኣንደ አሸባሪ በመፈረጅ፤ ቢሮዋቸውን በወታደሮች በመዝረፍና የጠሩትን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በጠብመንጃ ኣስፈራርቶ በማስተጋጎል ኣምባገነንነቱን ኣስመስክሮዋል:: በመቀጠልም በአንድነት ፓርቲ ላይም ተመሳሳይ ድርጊት በመፈጸም ለማዳከም ኢሰብአዊ ድርጊቱን ቀጥሎበታል:: ስለሆነም ወያኔ በጠመንጃ ስልጣን ላይ ከተቀመጠ ጀምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ መብቶቹን ለማስከበር ያላሰለሰ ትግል እያካሄደ ቢገኝም ወያኔ ሕዝቡን በጡንቻው እያስፈራራ ይገኛል ::ስለሆነም እስከ አሁን የተደረገው የትግል መስዋትነት ብዙ ዋጋ ቢያስከፍለንም አሁንም የሚፈለገውን ድል ለማምጣት የተለያዩ የትግል ስልቶችን በመጠቀም የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች በጋራ ተቀራርቦ በመስራት የፓርቲዎቹን አላማና የተለያዩ መረጃዎችን ሰብስቦ ወደ ህዝቡ ለማድረስ የሚያስችል ጠንካራ ተቋም መፍጠር ይጠበቅብናል እንዲሁም አባላቶችና ደጋፊዎችን ማጠናከር አባላቶችና ደጋፊዎች በገንዘብም ሆነ አስፈላጊ በሆነው ሁሉ ከፍተኛ ድጋፍ ማድረግ:: የወያኔን ዘረኛና ፋሽስታዊ የአገዛዝ ስርአት ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከስልጣን ለማስወገድ በመላው ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የእኩልነትና የፍትህ ጥያቄዎች ከሁሉም አቅጣጫ እየጎረፈ ይገኛል:: ማንኛችንም የሀገሬ ሠላምና ደህንንት ይመለከተናል የምንል ግለሰቦች የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች በጋራ ተሰባስበን የተቀጣጠለውንና እየተፋፋመ የመጣውን ታላቅ የህዝብ አመፅ በሁለንተናዊ የትግል እስትራቴጂ እንዲታገዝ አድርጎ የወያኔን የማፊያ ስርአት ከጫንቃችን ላይ አስወግደን እኩልነት ፍትህ ዲሞክራሲና እውነተኛ ፌደራላዊ ስርአት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመገንባት ከሌላው ግዜ በበለጠ መረባረብ ይጠበቅብናል:: የወያኔን ሀገር የማፍረስ የመዝረፍ ታሪክን የማበላሸትና የማጥፋት ተልኮውን አሁን ተባብረን ለማስቆም የተጀመረውን ትግላችንን እናጠናክር!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

advertisment

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here