ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት ጨካኝ አምባገንን መንግስትና የመንግስት ስርአቶች አስተናግዳለች::እነዚህም ስርአቶችን ለማስወገድ ከፍተኛ መስዋትነት ተከፍሉል አሁንም እየተክፈለ ይገኛል:: አሁን ኢትዮጵያን አስተዳድራለው የሚለው የወያኔ ቡድን ከሁሉም የባሰውንና በታሪኩ አይቶ የማያውቀውን ከፍተኛ ግፍ በደል ጭቆናና ውርደት በሕዝቡ ላይ እያደረሠበት ይገኛል:: አምባገነኑና ፋሽስታዊው የወያኔ ቡድን ላለፉት 22 አመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እጅግ በጣም አስከፊና ሁዋላ ቀር የህዝብን ጥቅም የማያስጠብቅ ጭከናና ኢሰብኣዊ የአገዛዝ ስርአት በመጫን የስልጣን ዕድሜውን ማራዘም አገርን ማፈራረስና የኢትዮጵያዊነትን ታሪክና ባህልን የማጥፋት ተልኮውን መፈጸም እና የህዝብን የሀገር ሀብት መዝረፍ በስፋት እየፈጸመ ይገኛል:: ህዝቡን በጠብመንጃ በማስፈራራትና ከታች የተዘረዘሩትን ተፈጥሮዊና ህገመንግስታዊ መብቶችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመከልከል የባንዳነት እኩይ ተግባሩን በመፈፅም ላይ ይገኛል::
1. ኢትዮጵያውያንን በመከፋፈል በጋራ ችግሮችን እንዳንፈታ ማድረግ ህዝቦችን በዘር በብሄር በቋንቋ በሀይማኖት በቀለም ብሎም ጎጠኝነትን በማስፋፋት እንዲለያዩ ማድረግና ክፍተኛ የጥላቻ ፖለቲካ ቅስቀሳ በህዝቡ ዘንድ ማሰረጨት:: እርስ በእርስ እንዳይስማሙ አንድነት እንዳይፈጥሩ ማህበራዊ ፖለቲካዊና እኮኖሚያዊ ችግሮቹ እንዳይፈቱ የሀገር ውስጥና የውጭ ጥላቶቹን ለመታገል አቅምና ስምምነት እንዳያጎለብት በዘር ፖለቲካ እንዲወጠሩ ማድረግ ከአንዳንድ ብሄረሰብና ሀይማኖተኞች ለግል ጥቅማቸው ያደሩትን ጥቂት ግለሰቦችን አቅፎ እምነትህ ባህልህ እና ጥቅምህ ተከብሮልሀል ብሎ በህዝብ ላይ መሳለቅ::
2. የሰውን ልጅ ተፈጥሮዋዊና ህገመንግስተዊ መብቶችን መከልከል በርካታ የህዝብን ተፈጥሮዊና ህገመንግስታዊ መብቶችን የመናገር የመፃፍ የመሰብሰብ በቡድን የመደራጀት ሀሳብን በአደባባይ ወጥቶ የመግለጽ በሀገሩ ላይ የመሬት ባለቤት መሆን የፈለገውን እምነት መከተልና የመሳሰሉትን በኢትዮጵያ ተፈፃሚ እንዳይሆኑ ማድረግ ወይንም በመሸራረፍና ለጥቂት የወያኔ አባላትና ደጋፊዎች ብቻ ተፈፃሚነት እንዲሆን ማድረግ::
3. በሕብረተሰቡ ተቀባይነትና ተሰሚነት ያላቸውን ግለሰቦች ማጥፋት ታዋቂና ለወደፊት ለአምባገነኑና ለፋሽስቱ ለወያኔ ቡድን የስልጣን ቆይታ አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ የሚያስባቸውንና በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትና ታማኝነት ያላቸውንና አላቸው ብሎ የሚጠረጥራቸውን የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎችን አባላቶችን ደጋፊዎችንና የደጋፊ ቤተሰቦችን ምሁሮችን መምህራኖችን ጋዜጠኞችን ዘፋኞችን ነፃ አሳቢ ዜጎችንና በተለያዩ የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን በአሸባሪነት በመፈረጅ በማስፈራራትና በእስር በማሰቃየት በአካልና በስነልቦና ላይ ጉዳት ማድረስ ንብረትን መውረስ መዝረፍ ማውደም አስፈራርቶ ከሀገር እንዲሰደዱ ማድርግ የት እንደደረሱ እንዳይታወቅ ማድረግ መግደልና ሌሎችንም የመሳሰሉ ወንጀሎችን በመፈፅም ሀገር የማፈራረስ ህዝብንና ሀገርን የማዋረድና ማቆሚያ የሌለው ኢሰብአዊ የባንዳነትተልኮውን መወጣት::
4. ስለሰብአዊ መብት መልካም አስተዳደር እና የሕግ የበላይነት ግንዛቤ እንዳይኖረው ማድረግ ለህዝብ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ለምሳሌ በሰብአዊ መብት በመልካም አስተዳደር በህግ የበላይነትና የመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ መጥነኛም ሆነ ጥልቅ ግንዛቤ እንዳያገኝና እንዳይኖረው ተግተው በመስራት ህዝቡ በዲሞክራሲያዊ ስርአቱ ግንባታ ላይ ምንም አይነት ተሳትፎ እንዳይኖረው ማድረግ:: ስለ ሰብአዊ መብት መልካም አስተዳደር የህግ የበላይነትን ለህዝቡ በማስተማር ላይ የተሰማሩትን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ነፃ ጋዜጦች የራዲዮና የቴሌ ፕሮግራሞችን ሆን ብሎ የተለያዩ አፋኝና ሰንካላ እንዲሁም የብዙሀኑን መብት የሚያቀጭጩ የጥቂት ቡድኖችን ስልጣን የሚያፋፋ ህጎችንና መመሪያዎችን አውጥቶ ለህዝቡ እውነተኛ መረጃ እንዳይደርስ ማድረግ ህዝቡም መብቶቹን እንዳያውቅና እንዳይጠቅም ማድረግ::
5. የሐገር ሐብትን ለባእዳን አሳልፎ መስጠት የኢትዮጵያን ህዝብ የሀገር የመሬትና የንብረት አልባ አድርጎ የወያኔ አባላት ብቻ የመሬትና የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ማድርግ:: ሀገርንና መሬትን ለባእዳን መሸጥና ለጎረቤት ሀገሮችም ትላልቅ መሬቶችን ቆርሶ መሸጥና አሳልፎ መስጠት እኛ በቅርጽና በመጠን የምናውቃትን ታሪካዊ ኢትዮጵያን ማጥፋት ህዝቡም በሀገሩ ላይ ስለ መሬት እንዳይጠይቅ በጠመንጃ ማስፈራራትና በሕዝብ ላይ ንቀቱን መግለፅ:: (ወደሚቀጥለው ገጽ ዞሯል)