አዲሱ ተስፋዬ ለደጀሰላም እንደጻፉት
መነሻ
ይህንን ጽሑፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ሰንደቅ ጋዜጣ በሚያዝያ 1/2006 ዓ.ም እትሙ ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ያወጣው ቃለ መጠይቅና ሐተታ ነው [i]:: በዜናው ላይ ስማቸው የተጠቀሰው ሦስቱም አስተያየት ሰጪዎች “ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ነው:: ስለዚህም መንግሥት ሊያፈርሰው ነው ” የሚለው ወቅታዊ ዜና ምንጩ ከየት እንደሆነ ግልጽ እንዳልሆነ ጠቅሰዋል :: በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ ወርቁ ጉዳዩን “በሬ ወለደ ነው”ብለው ሲያጣጥሉት፤ የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ደግሞ ” የዚህ ወሬ ምንጩ ከየት እንደሆነ አናውቅም” ሲሉ ተመሳሳይ ነገር ተናግረዋል።
በ 1955 እ. ኤ. አ የተመሰረተውና መቀመጫውን በኔዘርላድና በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው Open Doors : Serving Persecuted Christians Worldwide [ii]የተሰኘው ግዙፍ ድርጅት 2013 እ. ኤ. ኣ ባወጣው World Watch List ላይ ክርስቲያኖችን በማሰቃየት በ63 ነጥብ ኢትዮጵያ 15ተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝና ለዚህም ስቃይ ዋና ተዋናይ ከሆኑት አካላት መካከል አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን እንደሆነ ጽፎ ሊስቱንም በመላው ዓለም በትኗል [iii]። ሙሉውን ይሄንን ተጭነው በደጀ ሰላም ብሎግ ያንብብ