Friday, September 29, 2023
HomeEthiopian Newsየዳውኪንስ እና አዲሱ ኢ-አማኝነት ብዥታ

የዳውኪንስ እና አዲሱ ኢ-አማኝነት ብዥታ

ግደይ ገብረኪዳን

big bang

ይህ ጽሑፍ በዊልያም ሌን ክሬግ የተጻፈው The New Atheism and Five Arguments for God ሲሆን ሰሞኑን ግዜው ደርሶ ነው መሰለኝ ከዚህ በፊት የከተማዋ የሕትመት ውጤቶች በኦሾ ሰደድ ተለብልበው እንደነበረው አሁን ደግሞ ዳውኪንስ የሚባል ሰደድ ካልለበለብኩኝ እያለ ስለሆነ እስኪ ስለ ሰውየው ፍልስፍና እንወያይ ዘንዳ ምሁሩ ያቀረቡትን ረዘም ያለ መጣጥፍ አሳጥሬ ላካፍላችሁ ወስኛለው። እነሆ።

እግዚአብሔር ለመኖሩ የሚያስረዱ ጥሩ መከራከርያዎች አሉ? አዲሶቹ ኢ-አማንያን (New Atheists) የሚባሉትስ እነዚህ መከራከርያዎች አይረቤ መሆናቸውን አሳይተዋል?
በሚገርም መልኩ አዲሶቹ ኢ-አማንያን ተብዬዎቹ ስለ እግዚአብሔር ሕልውና የሚቀርቡ መከራከርያዎች ላይ የሚሉት የላቸውም። በዚህ ፈንታ ስለ ሃይማኖት ውጤት በማውራት፣ ሃይማኖት ለሕብረተሰቡ ጥሩ ነው ወይስ መጥፎ የሚለው ጥያቄ ላይ ያተኩራሉ። የአንድ ሃሳብ ጥሩ ወይም መጥፎ ማሕበራዊ ተጽእኖ ስለ ሃሳቡ እውነተኛነት ማረጋገጫ ሊሆን ይችላል ወይ የሚለውን መጠራጠር ተገቢ ነው።

ከአዲሶቹ ኢ-አማንያን የእግዚአብሔር ሕልውና መከራከርያን ሊፈትሽ የሞከረው ሪቻርድ ዳውኪንስ ነው። በዓለም አቀፍ ሽያጭ ሰንጠረዥ ምርጥ ሁኖ የነበረው የእግዚአብሔር ብዥታ (The God Delusion) በሚለው መጽሐፉ።[1] መከራከርያዎቹን ለመፈተሽ መነሳሳቱ እውቅና ቢገባውም መከራከርያዎቹ ግን ባሳማኝ መልኩ ስህተት መሆናቸውን አሳይተዋል?
ማንኛውም መከራከርያ ዋጋ እንዲኖረው ሁለት ነጥቦች መሟላት አለባቸው፦ (1) መሰረተ እውነት (ሎጂክ) የጠበቀ መሆን አለበት፤ (2) ማስረጃዎቹ (ፕረሚስስ) እውነት መሆን አለባቸው። መከራከርያው ጥሩ ከሆነ፣ መደምደሚያው ከማስረጃው የተገኘ ነው ማለት ነው። ማንኛውም ነገር እውነት ለመሆኑ ሙሉ ለሙሉ ሁሌም እርግጠኛ መሆን ስለማይቻል፤ ጥሩ መከራከርያ እንዲባል ከነዚህ ሁለት ነጥብ ውጪ ማስረጃው እውነት ነው እንድንል አመክንዮ (ሪዝን) ያስፈልገናል። በሌላ አነጋገር አንድ ማስረጃ ስንቀበል ከተቃራኒው ጋር በማነጻጸር የትኛው ይበልጥ እውነት ሊሆን ይችላል የሚለውን እናመዛዝናለን። ጥሩ መከራከርያ ተቀባይነት የሚኖረው ማስረጃዎቹ ከተቃራኒው በላይ የተሻለ ትክክለኛነት ያላቸው ሁኖ ሲገኝ ነው። ሙሉውን በሉላዊ ሴራ የተሸሸጉ ታሪኮች ገጽ ላይ ያንብቡ

advertisment

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here