ምንም እንኳን ወያኔን እንቃወማለን የሚሉ ድርጅቶች ሁሉ ተቃዋሚ ሃይሎች በመባል በአንድ ጎራ ተጠቃለው ይታወቁ እንጅ በውስጣቸው የተሰሉፉት ሃይሎች አንድ አይነትየትግል ስልትም ሆነ ብሄራዊ ራዕይ ያላቸው እንድልሆኑ ግልፅ ነው። ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ በጥገና ለውጥ ስርዓቱ እንዲሻሻል ማስገደድ ይቻላል የሚሉ፣ ሌሎች ደግሞ ስርዓቱ መቀየር አለበት የሚሉ፣ ነገር ግን የሃገሪቱን ሉአላዊነት ግምት ውስጥ የማያስገቡና የባዕዳንን የቆየ ተፅዕኖ በአዲስ ቀለም ለማስቀጠል የሚፈልጉና ዴሞክራሲን ከይስሙላ ምርጫ ጋር ቀላቅለው የሚያዩ፤ ጥቂቶች ደግሞ መገንጠልን በግልፅ እሚያራምዱ ወይም ይህንኑ ዓላማ በአዲስ ቋንቋ አለዝበው ሁኔታው እስኪመቻች የሚጠብቁና ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ነን ቢሉም እነዚህኑ ክፍሎች የሚያግዙና የሚያበረታቱትንም ያጠቃልላል። ከነዚህ ሁሉ ተለይተው የቆሙት ሃይሎች ደግሞ፣ ያለው አገዛዝ ከስረ መሰረቱ መነቀል ያለበት ብሄራዊ ጠላት በመሆኑ የሚያምኑና፤ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚገነባው፣ ህዝብ የስልጣን ባለቤት መሆኑ የሚረጋ ገጠው፣ እንዲሁም የሀገሪቱ አንድነትና ሉአላዊነነት የሚጠበቀው ስር- ነቀል በሆነ ለውጥ ብቻ ነው በሚል የሚገፉትን በሌላ በኩል የያዘ ሰፊ ጎራ ነው።
በትግል ታክቲክ ደረጃም እነዲሁ ከሰላማዊ መንገድ ውጪ ያሉ ሌሎች የ ትግል አማራጮችን ውድቅ የሚያደርጉ ሃይሎች በአንድ በኩል፣ ትግሉ የሚቻለውን አማራጭ ሁሉ ከመጠቀም መገደብ የለበትም ስለዚህ ሁለገብ የሆነ የትግል ስልት መያዙ ያዋጣናል የሚሉ በሌላ በኩል ይገኙበታል። በመጀመሪያው ስልት ላይ የሚነሳው ጥያቄ ግን ለምን ይህን አካሄድ መረጣችሁ ሳይሆን፣ በያዛችሁት መንገድ ቆርጦ ለመታገል ዝግጁ ናችሁ ወይ? የሚል ነው። ሰላማዊ ትግልስ ከመቸ ወዲህ ነው መጀመሪያውና መጨረሻው በአምባገነኖች ፈቃድ የሚወሰነው? የሚለውንም ጉዳይ መጠየቅ ያሻል። ለሰላማዊ ትግል፡ስብሰባዎችን፣ ተቃውሞ ሰልፍን፣ ስራ ማቆምን፣ የኢኮኖሚ እቀባን፣ የሙት ከተማን፣ ወዘተ የመሳሰሉትን ሁሉ መጠቀም ግድ የሚል ከሆና በፈቃድ ውጣ ውረድ ከታሰረ ፣ ቃሉ ራሱ አዲስ ትርጉም ሊያስፈልገውነው። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ