ምንጭ : ጉዳያችን
ሰሞኑን በማኅበረ ቅዱሳን ላይ መንግስት እያደረሰ ባለው የማዋከብ ተግባር ጋር በተያያዘ ቤተ ክርስቲያንን ለዘመናት ሲገዳደራት የነበረው የተሃድሶ አቀንቃኞች በውጭ በሚገኙ አንዳንድ ብሎጎቻቸው ላይ ከመንግስት ጋር እየተደረቡ በውጭ ላለው ማኅበረሰብ ስለ ጉዳዩ ገለልተኛ መስለው ማኅበረ ቅዱሳንን ለመንቀፍ ይሞክራሉ።
ስለ ተሃድሶ እና ማኅበረ ቅዱሳን ”ክርስቲያን ሳይንስ ሞኒተር” የተባለው ጋዜጣ ጁን 8/2000 ዓም ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ የተሃድሶ እንቅስቃሴ እንዳይሳካለት ያደረገው ምክንያት ምን እንደሆነ ሲገልፅ እንዲህ ይላል – ” የተማረ እና ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል ከፍተኛ ቅናት ያለው የወጣት ኃይል ማኅበረ ቅዱሳን በ 21ኛው ክ/ዘመን ዘልቃ መሄድ ትችል ዘንድ እየተጋደለ ስለሆነ ነው ” የጥቅሱ መጨረሻ።
ተሃድሶ ምንድን ነው? ከእዚህ በታች ያለውን ኦድዮ ላይ ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገኝ ለብስራት ራድዮ የሰጡትን ቃለ መጠይቅ ያዳምጡ።