ሃራ ዘተዋህዶ ላይ የወጣ
- ሥርዐቱ በተለይም መንግሥታዊ ሥልጣናቸውን ለሃይማኖታዊ ተልእኮ የሚጠቀሙ ሓላፊዎችና አማሳኝ የደኅንነት ግለሰቦች አሁን በተያዘው መንገድ ቀጥለው ማኅበረ ቅዱሳንን አላግባብ ወደ መገዳደር ብሎም ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አማሳኝ ግለሰብ ሓላፊዎች ጋራ ተባብረው ወደ ማፍረስ የሚሸጋገሩ ከኾነ ያለምንም ጥርጥር የተቃውሞው ጎራ ይጠናከራል፡፡ ይህም አገሪቱን በልማታዊ ዴሞክራሲያዊ የአውራ ፓርቲ ሥርዐት ለአርባና ኃምሳ ዓመታት እመራለው ለሚለው ገዥው ፓርቲ ግብዓተ መሬት አፋጣኝ ምክንያት ሊኾን እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ይስማማሉ፡፡
- በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ሃይማኖታዊና ምጣኔ ሀብታዊ ፍላጎት ያላቸው የገዥው ፓርቲ ባለሥልጣናትና ጥቂት አማሳኝ የደኅንነቱ ሰዎች ተቋሙን አፍርሶና ቤተ ክርስቲያንን በሒደት አዳክሞ በመቆጣጠር አልያም በታትኖ ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን ማስረከብ ቀላል እንደኾነ ያስባሉ፡፡ በአንጻሩ ‹‹በምድር ላይ ሊሳኩ ከማይችሉ ነገሮች አንዱ ይኼ የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ምኞት ነው፤›› የሚለው አንድ የቀድሞው የማኅበሩ ሥራ አመራር አባል እንደሚያሳስበው፣ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ የማኅበሩ አባላትና ደጋፊዎች፣ ማኅበሩ በግቢ ጉባኤያት አንፆ መስቀል በአንገታቸው አስሮ የሸኛቸው በብዙ መቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ምሩቃን፣ ኦርቶዶክሳውያን ምሁራንና በማኅበሩ ስኬታማና ተጨባጭ አገልግሎት የቤተ ክርስቲያን ፍቅር ያደረባቸው ምእመናን ኹሉ ለዘመናት እየመነዘሩ ማንኛውንም የቤተ ክርስቲያኒቱን ተግዳሮቶች የሚመክቱበት መንፈሳዊ ኃይል እንዳላቸው በቅጡ መረዳት ያሻል፡፡
- በርካታ አገራዊ አጀንዳዎች አሉኝ በማለት ሕዝቡን ለሕዳሴ የሚያነሣሣው መንግሥት፣ በተለይም የፀረ አክራሪነቱን ትግል በቅድመ ግንባር እንዲመራ ፖሊቲካዊ ተልእኮ የተሰጠው አካልና ሓላፊዎቹ፣ መካሪ እንደሌለው የእብድ ሥራ ከመሥራታቸውና እጃቸውን ወደ ብልሽት ከመዘርጋታቸው በፊት ነገሮችን በርጋታ ማጤንና በግልጽ ውይይት ማመን ይበጃቸዋል፡፡ ሙሉውን ሃራ ዘተዋህዶ ላይ ለማንበብ ይሄን ይጫኑ