መምህርት ኑኃሚን ዋቅጅራ 28 ዓመቷ ሲሆን ተወልዳ ያደገችው በአዲስ አበባ መሳለሚያ አካባቢ ነው፡፡ ዕድገቷ በቤተ ክርስቲያን አካባቢ በመሆኑ ለግዕዝ ትምህርቷ መነሻ ሆኗታል፡፡
(ሪፖርተር) በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቅፅር ግቢ በቄስ ትምህርት የተጀመረው ትምህርቷ ዛሬ የግዕዝ መምህርት እንደትሆን አድርጓታል፡፡ የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት በሚሰጥበት አቡነ ጐርጐርዮስ ትምህርት ቤት ከአንደኛ እስከ 10 ክፍል የሚያገለግል የመማርያ መጻሕፍት ከዚህ ቀደም አዘጋጅታ አበርክታለች፡፡ የካቲት 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ደግሞ ማንኛውም የግዕዝ ቋንቋን ማወቅ የሚፈልግ የሚማርበት ‹‹ማህቶተ ጥበብ ዘልሣነ ግዕዝ›› የመጀመሪያ ክፍል መጽሐፍ አስመርቃለች፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ግዕዝን የሚያመሰጥሩ የሚያስተምሩና እንደ እማሆይ ገላነሽ ዓይነት ሴቶች ቢኖሩም ከግዕዝ መምህርነቷ በተጨማሪ በመጽሐፍ ከትባ ለማስቀመጥ የመጀመርያዋ ሴት መሆኗን መጽሐፉ በተመረቀበት ዕለት የተገኙት የግዕዝ መምህሩ ዜና እንዳለው ተናግረዋል፡፡ መምህርት ኑኃሚን በአማርኛ እንግሊዝኛ ቋንቋ ከቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ዲፕሎማ፣ በሥነ መለኮት ከቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ዲፕሎማዋን አግኝታለች፡፡ በግዕዝ ሥራዎቿ ዙርያ ምሕረት ሞገስ አነጋግራታለች፡፡ ሙሉውን በሪፓርተር ላይ ያንብቡ …