(ቦርከና) የኢትዮጵያ ራዲዮ እና ቴሌቪዢን ድርጂት በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኝ የኮሚኒኬሽን ካምፓኒን ለሳተላይት ስርጭት እንደመረጠ ቴሌኮም ፔፐር የተባለ ድረ-ገጽ ዘገበ
የሳተላይት ስርጭቱ የተፈለገው የኢትዮጵያ ሬዲዮ እና ሳተላይት ስርጭት የኢቲቪን ስርጭት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማሰራጨት ነው፤ እንደዘገባው።
የተመረጠው ካምፓኒ ሳትሊንክ የሚባል ሲሆን ተቀማጭነቱ በመካከለኛው ምስራቅ ነው። ሳትሊንክ የኢቲቪን ስርጭቶች በተለያዮ ባንዶች በአፍሪካ፤ በመካከለኛው ምስራቅ ፤ በመካከለኛው ምስራቅ እና በሰሜን አሜሪካ እንደሚያደርስ ዘገባው ይጠቁማል።
ድርጂቱ ከኢትዮጵያ ራዲዮ እና ቴሌቭዠን ድርጂት ስለተከፈለው ወይንም ስለሚከፈለው የአገልግሎት ዋጋ የተጠቆመ ነገር የለም። ሳትሊንክ ከነ ሮይተርስ እና ዮሮኒውስ ጋር በሸሪክነት እና በደምበኝነት የሚሰራ ድርጂት እንደሆነ የድርጂቱ ድረ-ገጽ ይጠቁማል።
አብዛኛው ሃገር ቤት ያለው ኢትዮጵያዊ አክብሮት እና ጥሩ ግምት የማይሰጠው የኢትዮጵያ ሬዲዮ እና ቴሌቭዥን ውጭ ባሉ ኢትዮጵያውያን ምን ያህል ተቀባይነት ይኖረዋል የሚለው ጥያቄ ቢሆንም ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በዲያስፓራ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ኮምፒዮተሮች በስፓይ ዌር እና ማልዌር ለሚያበለሻሽ ድርጂት ገንዘብ ከማውጣት ይልቅ ቆይቶም ቢሆን ለአሰራጭዎች እየከፈለ የራዲዮ እና የቴሌቭዥን ጣቢያዎቹን ስርጭት ለማድረስ መሞክሩ ይሻለው ይሆናል።