Wednesday, December 6, 2023
HomeSliderየ ፓትርያርኩ የለውጥ ተግዳሮትና ተስፋ - በአንደኛ ዓመት በዓለ ሢመት ዋዜማ

የ ፓትርያርኩ የለውጥ ተግዳሮትና ተስፋ – በአንደኛ ዓመት በዓለ ሢመት ዋዜማ

Addis Admas
አዲስ አድማስ

የብልሹ አሠራርና ሙስናን ችግር በዐደባባይ የተናገሩ የመጀመሪያው ፓትርያርክ ናቸው
ፓትርያርኩ ጽኑ አቋም ስለሌላቸው ለጣልቃ ገብነት የተመቹ ኾነዋል
ጣልቃ ገብነቶችን መቋቋምና የቅ/ሲኖዶሱን የውሳኔ ልዕልና ማስከበር ይጠበቅባቸዋል
ፓትርያርኩ ዙሪያቸውን መፈተሽ አለባቸው
ብቃት ያለው የአማካሪ መዋቅር ያስፈልጋቸዋል

የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም ፤ ለስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ምርጫ ከቀረቡት አምስት ዕጩዎች መካከል በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማትያስ በከፍተኛ ድምፅ መመረጣቸው ተነገረ። ሊቀ ጳጳሱ በቤተ ክርስቲያኒቱ የፓትርያርኮች ምርጫ ታሪክ ከፍተኛውን የመራጮች ድምፅ በማግኘት አሸናፊ መኾናቸው በተገለጸበት ወቅት የብዙዎችን ትኩረት በሳበ ኹኔታ በመስቀላቸው ሲያማትቡ ታዩ።
የወቅቱን ስሜታቸውን አስመልክቶ ‹‹ዜና ቤተ ክርስቲያን›› በተሰኘው መጽሔት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ÷ ‹‹ፓትርያርክ እኾናለሁ የሚል መንፈስ በውስጤ ስላልነበረ ውጤቱ ሲገለጽ እንዴት ነው ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ምንድን ነው ከሚል ደነገጥኩኝ፤ በዚያው ቅጽበት የተሰማኝ፣ እግዚአብሔር ይህን ታላቅ ሓላፊነት እንዴት እችለዋለሁ? በል አንተ ታውቃለህ፤›› የሚል እንደነበር አስረድተዋል፡፡
ከምርጫው ሦስት ቀናት በኋላ የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተከናወነው ሥርዐተ ሢመት÷ ለፓትርያርክነት መመረጣቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ጥሪ እንደኾነና ጥሪውን የተቀበሉት መኾኑን፣ መቀበላቸውም ለክብርና ለልዕልና ሳይኾን ለመሥዋዕት በመታዘዝ በመኾኑ የቅዱስ ሲኖዶሱን አባላት በመያዝ በጋራ እንደሚወጡት ያላቸውን እምነት ተናግረው ነበር፡፡ ቀሪውን ይህንን ማያያዣ በመጫን አዲስ አድማስ ላይ ያንብቡ

advertisment

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here