የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የበረራ ኃላፊ እንደሾመ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። አዲሱ ተሿሚ ካፒቴን ዮሃንስ ኃይለማርያም ሹመታቸው የጸደቀው ከትላንት ጀምሮ ነው።
ካፒቴን ዮሃንስ ኃይለማርያም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ትምህርት ቤት ምሩቅ እንደሆኑ እና በአየር መንገዱ ከሰላሳ ዓመት በላይ እንደሰሩ የአየር መንገዱ መግለጫ ይጠቁማል። በእነዚህ ዓመታት የበረራ እና ስልጠና ሃላፊም ሆነው ሰርተዋል።
ካፒቴን ዮሃንስ የተሾሙት በቅርቡ የኃላፊነቱን ስራ በለቀቁት ካፒቴን ደስታ ዘሩ ምትክ ሲሆን ፤ የአየር መንገዱ መግለጫ ካፒቴን ደስታ ዘሩ ስራቸውን የለቀቁት በራሳቸው ምክንያት ነው ይላል።
አዲሱ ተሿሚ ካፒቴን ዮሃንስ ኃይለማርያም የካፒቴን ደስታ ዘሩን “ቪዠን 2025” የሚባለውን የእድገት እቅድ ያስቀጥላሉ ሲል የአየር መንገዱ መግለጫ ጨምሮ ገልጿል።