Tuesday, November 28, 2023
HomeEthiopian Newsኢትዮጵያ እና ሱዳን የጋራ የድንበር ሰራዊት ለመመስረት ተስማሙ

ኢትዮጵያ እና ሱዳን የጋራ የድንበር ሰራዊት ለመመስረት ተስማሙ

ኢትዮጵያ እና ሱዳን የጋራ የድንበር ጥበቃ ሰራዊት ለመመስረት እንደተስማሙ ሱዳን ትሪቢዮን ዘግቧል። ስምምነቱ የተደረገው የወታደራዊ ቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባ በተጠናቀቀበት ወቅት ሲሆን ፤ የሱዳኑ መከላከያ ሚኒስተር አብዱል ራሂም መሃመድ ሁሴን እና የኢትዮጵያው መከላከያ ሚኒስተር ሲራጂ ፈርጌሳ ስምመነቱን ፈርመዋል።

በአመራር ደረጃ በሁለቱ ሃገሮች የሚደረጉ መደበኛ ስብሰባዎች ላው ያለ የጋራ መተማመን ፈጥረዋል ሲሉ የሱዳኑ መከላከያ ሚኒስተር ተናግረዋል። የትብብሩ ደረጃ የጋራ የድንበር ሰራዊት የመፍጠር እና የጋራ ስልጠና መስጠት ደረጃ ላይ መድረሱንም የሱዳኑ መከላክያ ሚኒስተር ጨምረው ገልጸዋል።

የመከላከያ ሚኒስተር ሲራጅ ፈርጌሳ በኮሚቴው ስራ ለመሳተፍ ሱዳን የገቡት ባለፍው ረቡዕ ነበር።

አብዱል ራሂም መሃመድ ሁሴን እና ሲራጂ ፈርጌሳ የስብሰባውን ቃለ-ጉባዔውን ፈርመዋል። ስምምነቱ የጋራ የድንበር ሰራዊት ምስረታን፤ የሰላም ጥበቃን ፤ የመረጃ ልውውጥን እና “ህገ-ወጥ” ያሏቸውን ቁጥጥር ማድረግን እንደሚጨምር የሱዳን ትሪቢዮን ዘገባ አመልክቷል።

ወያኔ መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ለሱዳን መሬት እንደሰጠ በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አንድነት ለፍትህ እና ለዲሞክራሱ ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ ተሰጡ የተባሉትን ቦታዎች በመዘርዘር ምስክርነት እንደሰጡ የሚታወስ ነው።

advertisment

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here