Ethiopian Airlines Copilot mother speak out
W/o Hizbale Seyoum, Co-pilot Hailemedhin ‘s mother, gave brief interview. Simply, she is very sharp!
Video – initially posted on facebook page of Dawit Solomon
Ethiopian Airlines Copilot mother speak out
W/o Hizbale Seyoum, Co-pilot Hailemedhin ‘s mother, gave brief interview. Simply, she is very sharp!
Video – initially posted on facebook page of Dawit Solomon
እኛ በተማርነዉ ትምህርት ሳይሆን መማር ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ስለምንረዳ ነዉ ያስተማርነዉ
ስለ ረዳት ፓይለቱ ቤተሰቡ የሰጠዉን ምክኒያት የሚያጠናክር ተጨማሪ ሃሳብ
የችግሩ መፈጠር በሁሉም የቤተሰቡ አባላት ያልተጠበቀ ቢሆንም ታላቅ ወንድሙ በአሜሪካ ድምፅ ራዲዩ የአማረኛዉ ዝግጅት ክፍል ወላጅ እናቱ በዚህ ድህረ ገፅ የሰጡትን ቃለምልልስ አዳምጫለሁ እርሱ የሚለዉን ወደፊት የምንሰማዉ ሆኖ የቤተሰቡን ሃሳብ የሚያጠናክር አንድ ነገር ልጨምር አዉሮፕላኑ ዉስጥ ነበርን ያሉ ኢትዮዽያዊ በማህበረስብ ድህረ ገፅ እንደገለፁት በረራዉ የካቲት 9 ቀን 2006 ዓ/ም ከምሽቱ 4.00 ስዓት አካባቢ ነበር የተጀመረዉ በዚሁ እለት ደግሞ የኃይለመድህን አጎት የዶክተር እምሩ ስዩም የ40 ቀን መታሰቢያ ሰሜን ጎንደር ዞን አለፋ ወረዳ ሻሁራ ከተማ እንዲሁም አዲስ አበባ በመኖሪያ ቤቱ ይከናወን ነበር፤ በዚህም አብዛኛዉ ቤተሰብ በተስካሩ ላይ እንደነበረ ይታወቃል እርሱ ደግሞ ጉዞ ወደ ሮም ነበር እናም የጎዞዉና የአጎቱ መታሰቢያ መገጣጣም ቤተሰቡ እንደሚለዉ ከአጎቱ ድንገተኛ አሟሟት ጋር በተያያዘ የኃይለመድህን ችግር ምን እንደነበረ አንድ ማሳያ እንደሚሆን እግምታለሁ ።
በሌላ በኩል ግን ችግሩ ባይፈጠር ጥሩ ነበር ከተፈጠረም በኃላ በሰዉ ህይወትም ይሁን በንብረት ላይ አደጋ አለመፈጠሩ ጥሩ ሆኖ ከዚህ ችግር በተጔዳኝ ኢትዮዽያዊያን ቤተሰቦች ስለልጅ አስተዳደግና አስተምሮ የተሻለ ደረጃ ማድረስ ምን ይማራሉ፤ ከዚህ ቤተሰብ ዉስጥ ትምህርት ቤት ከገቡ 11 ልጆች ከአንዷ በስተቀር ሁሉም በከፍተኛ ዉጤት ወደ ዩኒቨርስቲ መግባታቸዉ ዶክተሮች ኢንጅነሮችና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራማሪ ልጆችን አፍርተዋል።ሁሉም ወላጅ ልጅ ያስተምራል ነገር ግን በዚህ መንገድ ለስኬት መብቃት እንዴት እንደሚቻል ከእናቱ ቃለ መጠይቅ መማር ብንችል ለሁላችንም ይጠቅማል።
i felt about the speech of hailemedin ,s mother.she is enough brilliant by nature. god may bless hailemedin’s families