(ቦርከና) አሊ አህመድ ሁሴን እና ሱሉብ አብዲን የሚባሉ ሁለት የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር የልዑካን ቡድን አባላትን በናይሮቢ በሚገኝ ምግብ ቤት ጠልፈዋል በሚል ክስ በኬኒያ መንግስት ታስረው የነበሩ ሁለት የወንጀል ምርመራ ፓሊስ አባላት ፍርድ ቤት ቀርበው በዋስ ተለቀዋል።
አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ዶሪን ሙልክዮ የተባሉት ዳኛ ሁለቱን የፖሊስ አባላት በሁለት ሚሊዮን የኬኒያ ሽልንግ ዋስ ነው የለቀቁዋቸው፡፡
“የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር” የኬኒያን መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የሚደረገውን ድርድር በገለልተኝነት ለማስተናገድ ኃላፊነት እንደመውሰዱ መጠን ባለፈው ወር በናይሮቢ የተደረገውን የጠለፋ ተግባር በጥልቀት እንዲያጣራ እና የኢትዮጵያ መንግስት ተጠላፊዎቹን እንዲለቅ እንዲጠይቅ ጠይቋል።