የዴትሮይትን ከተማ በስደተኞች ለማሟላት ታስቧል

በአማሪካ ሚቺጋን ስቴት የምትገኘው የዴትሮይት ከተማ ከተማዋ ከደረሰባት የገንዘብ ኪሳራ ጋር ተያይዞ ያሽቆለቆለባትን የህዝብ ቁጥር በስደተኞች ለመሙላት ሃሳብ እንዳላት በቅርቡ በኒዮርክ ታይምስ ላይ የወጣ ዘገባ ያመላክታል።

የከፍተኛ ትምህርት ዲግሪ ላላቸው ፤ በሳይንስ መስክ የተለየ ችሎታ ላላቸው ፤ ለንግድ እና ለጥበብ ሰዎች ከሚሰጠው የቪዛ ፕሮግራም ተያይዞ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ እስከ 50 000 የሚደርሱ ስደተኖችን ወደ ከሰረችው ዴትሮይት ከተማ ለማስፈር ከፌደራል መንግስቱ እገዛ የመጠየቅ ሃሳብ እንዳላቸው የሚችጋኑ ሃገር ገዠ ሪክ ስናይደር ተናግረዋል።

ዘገባው የዴትሮይት ከተማ በ1950ዎቹ ወደ 1.8 የሚጠጋ የህዝብ ቁጥር እንደነበራት አስታውሶ አሁን ሰባት መቶ ሺህ ብቻ ነዋሪዎች እንዳሏት ጠቁሟል።

ባለፈው ዓመት ከተማዋ ኪሳራ በሚደርስ ጊዜ የሚገኝ የኪሳራ ዋስትና እንትጠይቅ የፈቀዱት የሚችጋኑ ሃገረ ገዥ ሪክ ስናይደር “ድሮስ ቢሆን ሃገራችንን ታላቅ ያደረግናት በስደተኞች አይደለም ወይ?” የሚል አስተያየት እንደሰጡ ዘገባው ጨምሮ ገልጿል።

ምንጭ ኒውዮርክ ታይምስ

Leave a Reply

Your email address will not be published.