አንድነት ለፍትህ እና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ሱዳን በቅርቡ ስለተሰጣት ተጨማሪ የኢትዮጵያ መሬት የፌደራል እና የክልል ሶስት ባለስልጣናትን ማብራሪያ ጠይቋል። ፓርቲው ለ
ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ በጻፈው እና ለፌደራል እና ለክልል ባለስልጣናት ግልባጭ ባደረገው ደብዳቤ የኢትዮጵያ ሱዳን ወሰን ማካለል ጉዳይ ከውጪ እና የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን መስማቱን ገልጾ ፤ ጉዳዮ አብይ ሃገራዊ ጉዳይ ሆኖ ሳለ ህዝባዊ ውይይት ሳይደረግበት ከሕዝብ ተሰውሮ መካሄዱ ከመንግስት የማይጠበቅ መሆኑን ገልጾ ሶስት ጥያቄዎችን አንስቷል።
አንድነት የጻፈውን ደብዳቤ እዚላ ላይ ተጭኖ ማግኘት ይቻላል።