Thursday, June 1, 2023
HomeEthiopian VideoViral VideosInterview with the former Ethiopian PM Fikre Selassie Wegderes - part 2...

Interview with the former Ethiopian PM Fikre Selassie Wegderes – part 2

Interview with the former Ethiopian PM Fikre Selassie Wegderes – part 2

በአሸናፊ ወገን (ህወሓት/ኢህአዴግ) የተሰጠውን ትረካ ከ “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ”ትውልድ መጽሃፍ እስከ በቋሚነት በመገናኛ ብዙሃን ቅስቀሳ በሚመስሉ ፕሮግራሞች የተሰጡትን ትረካዎች ሰምተናል። ምንም እንኳ ደርግ ከወታደር ቁጥር አንጻር እንደሚባለው ከአፍሪካ ሀገራት በቀዳሚነት የሚቀመጥ ቢሆንም ፤ የፓለቲካ አደረጃጀቱ እና መስተዳድሩ ግዙፍነቱን ይገልጻል አይገልጽም የሚለው ጥያቄ ያስነሳል። ለአማጺያኑ የሚሰሩ የመስተዳደሩ አካላት እንደነበሩ ይነገራል ፤ ለውጭ ኃይሎች የሚሰሩ የመስተዳድር አካላት እንደነበሩ ይነገራል። ስለደርግ የሚሰጠው የ “ግዙፍነት” ትረካ የአማጺዎቹን ወታደራዊ ድል አላገዘፈም ማለት አይቻልም። ምናልባት የደርግ “ግዙፍነት” የትረካቸው አካል የሆነበት ምክንያትም ይሄ ሊሆን ይችላል። የሆነ ሆኖ የአሸናፊዎቹን ትረካ በተደጋጋሚ የሰማነውን ያህል የተሸናፊዎቹን ትረካ እስከዛሬ ብዙ አልሰማንም። ፍቅረ ስላሴ ወግደረስ በSBS በሰጡት ቃለ ምልልስ ሁለተኛ ክፍል መንግስታቸው በህወሓት/ ኢህአዴግ የተሸነፉበትን ምክንያት ያብራራሉ። ምን ያህል ያስማማል?

advertisment

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here