Tuesday, December 5, 2023
HomeEthiopian Newsየደቡብ አፍሪካ መንግስት በኔልሰን ማንዴላ መታሰቢያ ሃውልት ጆሮ የተቀመጠ ጥንቸል እንዲነሳ...

የደቡብ አፍሪካ መንግስት በኔልሰን ማንዴላ መታሰቢያ ሃውልት ጆሮ የተቀመጠ ጥንቸል እንዲነሳ አዘዘ

Posted on BBC /AFP
Posted on BBC /AFP

 

በፕሪቶሪያ የመንግስት ማዕከል ዮኒየን ህንጻ አካባቢ ለኔልሰን ማንዴላ መታሰቢያ በማንዴላ ምስል ተቀርጾ በቆመ ዘጠኝ ሜትር ከፍታ ባለው ሃውልት፤ በኔልሰን ማንዴላ ቀኝ ጆሮ ውስጥ በፊርማ መልክ የተቀመጠ የጥንቸል ምስል እንዲነዛ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ትዕዛዝ አስተላልፏል።

የደቡብ አፍሪካ ስነ ጥበብ እና ባህል ሚኒስተር ቃል አቀባይ ሚስተር ሞጎዲሪ ለቢቢሲ “ፎከስ ኦን አፍሪካ” ፕሮግራም እንደተናገረው ማንዴላ በጆሮአቸው ውስጥ ጥንቸል የሚባል ነገር ስላልነበረ በሃውልታቸው ጆሮ ጥንቸል ማስቀመጡ አግባብ አይደለም ብሏል። ሰው የመታሰቢያ ሃውልቱን እንደ ተስፋ ምልክት እንጂ ፤ ከጥንቸል ጋር በተያያዘ መልኩ እንዲያየው አንፈልግም ሲል ቃል አቀባዮ ጨምሮ “ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ” ገልጾአል።

ሃውልቱን የሰሩት አንድሬ ፕሪንስሎ እና ሩሃን ጃንስ ቫን  ቩረን የሚባሉት የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያዎች (sculptors) ጥንቸሉን ማንዴላ ጆሮ  ውስጥ ያስቀመጥነው የስነ-ጥበብ እና ባህል ሚኒስተር ፊርማችንን በመታሰቢያ ሃውልቱ ሱሪ ላይ ለማስቀመጥ ፈልገን ከከለከለን በኋላ ነው ብሏል። የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያዎቹ ጥንቸሉ የንግድ ምልክት ፊርማ ነው ባይ ናቸው።  ፕሪንስሎ “ጆሮ ውስጥ የተደበቀው ትንሽ ጥንቸል ሃውልቱን የነሳው ነገር የለም። ጥንቸሉንም ለማየት ከርቀት አጉልቶ የሚያሳይ መሳሪያ ያስፈልጋል” ብሏል።

ሆኖም የባህል ሚኒስተር ቃል አቀባይ እንዳለው የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያዎቹ በማንዴላ ሃውልት የቀኝ ጆሮ ውስጥ ያስቀመጡት የጥንቸል ምስል የደቡብ አፍሪካን መንግስት እና የማንዴላን ቤተሰብ በማስቀየሙ ይቅርታ ጠይቀዋል።

በርቀት በሚያሳይ መሳሪያ (ባይናኩላር) ካልሆነ በስተቀር ጥንቸውሉ አይታይም የሚለው የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያው ምጸታዊ ማስተባበያ ለተንኳሽነታቸው የበለጠ ማሳያ የሚሆን ይመስላል።

 

advertisment

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here